በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
(በቀኝ እጅህ ግንባርህን፣ ደረትህን፣ የግራና የቀኝ ትከሻህን በመዳሰስ የመስቀል ምልክት አድርግ።)
1. SAY THESE PRAYERS... (እነዚህን ጸሎቶች በል...)
ሁሉን በሚችል ሰማይንና ምድርን በፈጠረ በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ ፤
የአብ አንድ ልጅ በሆነው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አምናለሁ ፤
እርሱ በመንፈስ ቅዱስ ተፀንሶ ፤ ከድንግል ማርያም ተወለደ ፤
በጴንጤናዊው ጲላጦስ ዘመን ተሠቃየ ፤ ተሰቀለ ፤ ሞተ ፤ ተቀበረ ፤
ወደ ሲኦል ወረደ ፤ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነሣ ፤ ወደ ሰማይ ዐረገ ፤
ሁሉን በሚችል በእግዚአብሔር አብ ቀኝ ተቀመጠ ፤
ያሉትንና የሞቱትን ሊፈርድ ዳግመኛ ይመጣል ፤
በመንፈስ ቅዱስም አምናለሁ ፤
የሁሉም በሆነችው በቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፤ በቅዱሳንም አንድነት አምናለሁ ፤
በኃጢአት ሥርየት ፤ በሙታን ትንሣኤ ፤ በዘላለም ሕይወት አምናለሁ ፤ አሜን።
በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ ፤
ስምህ ይመስገን ፤ መንግሥትህ ይምጣ ፤
ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነ ፤ እንዲሁም በምድር ይሁን ።
የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን ፤
እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል ፤ በደላችንን ይቅር በልልን ፤
ከክፉ ሁሉ ሰውረን እንጂ ፤ ወደ ፈተና አታግባን ።
አሜን።
ጸጋ የሞላሽ ማርያም ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን ፤
እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው ፤
ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ ፤
የሆድሽም ፍሬ ኢየሱስ የተባረከ ነው ።
ቅድስት ማርያም ያምላክ እናት ፤
ለምኚልን ለእኛ ለኃጢአተኞች ፤
አሁንም በሞታችንም ጊዜ ።
አሜን።
ለአብና ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይሁን ፤
አሁንም ዘወትርም ለዘለዓለሙ ።
አሜን።
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፡ በደላችንን ይቅር በለን ፤
ከገሃነም እሳት ሰውረን ፤
ሁሉን ነፍሳትንና በተለይም የአንተ ምሕረት የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማይ ውሰዳቸው ።
ጌታ አምላካችን ሆይ ፡ በአንተ እናምናለን ፤ እንሰግድልሃለን ፤ እንወድሃለን ፤ በአንተም ተስፋ እናደርጋለን ፤
ለማያምኑህ ፡ ለማይሰግዱልህ ፡ ለማይወዱህና በአንተም ተስፋ ለማያደርጉ ሁሉ ምሕረትህን ታደርግላቸው ዘንድ እንለምንሃለን ።
አሜን።
ኦ ንግሥት ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን ፤
የሕይወታችን ፤ የተስፋችን ጥዕምት የሆንሽ የምሕረት እናት ሆይ ፤
እኛ በጭንቀት ያለን የሔዋን ልጆች በዚህ በለቅሶ ቆላ በሐዘን እያቃሰትን እያለቀስን ፤ እንማጠንሻለን ።
በጸጋ የተሞላሽ ጠበቃችን ሆይ ፤ በምሕረት ዓይኖችሽ ተመልከችን ።
ከዚህ ዓለም ስደት በኋላ የሆድሽን ብሩክ ፍሬ ኢየሱስን አሳዪን ።
ኦ ርኅርኅት ፤ ኦ አፍቃሪ እናት ፤ ኦ ጥዕምት ድንግል ማርያም ።
አሜን።
Simply announce the mystery and read the verses before beginning the decade.
(e.g. "The third Joyful mystery is the Birth of Our Lord")
2. IN THIS ORDER... (በዚህ ቅደም ተከተል...)
INTRODUCTION
- 1. IN THE NAME... (የመስቀል ምልክት)
- 2. I BELIEVE IN GOD... (አምናለሁ)
- 3. OUR FATHER... (አባታችን ሆይ)
- 4–6. HAIL MARY... (3x - ሰላም ላንቺ ይሁን)
- 7. GLORY BE... (ክብር ለአብ)
- 8. O MY JESUS... (የፋጢማ ጸሎት)
THE FIRST DECADE
- 9. ANNOUNCE 1st MYSTERY (ምስጢሩን አውጅ)
- 10. OUR FATHER... (አባታችን ሆይ)
- 11–20. HAIL MARY... (10x - ሰላም ላንቺ ይሁን)
- 21. GLORY BE... (ክብር ለአብ)
- 22. O MY JESUS... (የፋጢማ ጸሎት)
THE SECOND DECADE
- 23. ANNOUNCE 2nd MYSTERY (ምስጢሩን አውጅ)
- 24. OUR FATHER... (አባታችን ሆይ)
- 25–34. HAIL MARY... (10x - ሰላም ላንቺ ይሁን)
- 35. GLORY BE... (ክብር ለአብ)
- 36. O MY JESUS... (የፋጢማ ጸሎት)
THE THIRD DECADE
- 37. ANNOUNCE 3rd MYSTERY (ምስጢሩን አውጅ)
- 38. OUR FATHER... (አባታችን ሆይ)
- 39–48. HAIL MARY... (10x - ሰላም ላንቺ ይሁን)
- 49. GLORY BE... (ክብር ለአብ)
- 50. O MY JESUS... (የፋጢማ ጸሎት)
THE FOURTH DECADE
- 51. ANNOUNCE 4th MYSTERY (ምስጢሩን አውጅ)
- 52. OUR FATHER... (አባታችን ሆይ)
- 53–62. HAIL MARY... (10x - ሰላም ላንቺ ይሁን)
- 63. GLORY BE... (ክብር ለአብ)
- 64. O MY JESUS... (የፋጢማ ጸሎት)
THE FIFTH DECADE
- 65. ANNOUNCE 5th MYSTERY (ምስጢሩን አውጅ)
- 66. OUR FATHER... (አባታችን ሆይ)
- 67–76. HAIL MARY... (10x - ሰላም ላንቺ ይሁን)
- 77. GLORY BE... (ክብር ለአብ)
- 78. O MY JESUS... (የፋጢማ ጸሎት)
CONCLUSION
- 79. HAIL, HOLY QUEEN... (ኦ ንግሥት ሆይ)
- 80. IN THE NAME... (የመስቀል ምልክት)
3. WHILE TOUCHING THESE BEADS TO KEEP TRACK OF YOUR PROGRESS...
4. AND SILENTLY MEDITATING ON THESE "MYSTERIES", OR EVENTS FROM THE LIVES OF JESUS AND MARY...
ሰኞ እና ቅዳሜ፡ የደስታ ምስጢራት (On Monday and Saturday: The Joyful Mysteries)
- First Decade (Steps 9–22): The Annunciation of Gabriel to Mary (ሉቃስ 1:26-38)
- Second Decade (Steps 23–36): The Visitation of Mary to Elizabeth (ሉቃስ 1:39-56)
- Third Decade (Steps 37–50): The Birth of Our Lord (ሉቃስ 2:1-21)
- Fourth Decade (Steps 51–64): The Presentation of Our Lord (ሉቃስ 2:22-38)
- Fifth Decade (Steps 65–78): The Finding of Our Lord in the Temple (ሉቃስ 2:41-52)
ሐሙስ፡ የብርሃን ምስጢራት (On Thursday: The Luminous Mysteries)
- First Decade: The Baptism of Our Lord in the River Jordan (ማቴዎስ 3:13-17)
- Second Decade: The Wedding at Cana, when Christ manifested Himself (ዮሐንስ 2:1-11)
- Third Decade: The Proclamation of the Kingdom of God (ማርቆስ 1:14-15)
- Fourth Decade: The Transfiguration of Our Lord (ማቴዎስ 17:1-8)
- Fifth Decade: The Last Supper, when Our Lord gave us the Holy Eucharist (ማቴዎስ 26:26-30)
ማክሰኞ እና ዓርብ፡ የሕማም ምስጢራት (On Tuesday and Friday: The Sorrowful Mysteries)
- First Decade: The Agony of Our Lord in the Garden (ማቴዎስ 26:36-56)
- Second Decade: Our Lord is Scourged at the Pillar (ማቴዎስ 27:26)
- Third Decade: Our Lord is Crowned with Thorns (ማቴዎስ 27:27-31)
- Fourth Decade: Our Lord Carries the Cross to Calvary (ማቴዎስ 27:32)
- Fifth Decade: The Crucifixion and Death of Our Lord (ማቴዎስ 27:33-56)
ረቡዕ እና እሑድ፡ የክብር ምስጢራት (On Wednesday and Sunday: The Glorious Mysteries)
- First Decade: The Glorious Resurrection of Our Lord (ዮሐንስ 20:1-29)
- Second Decade: The Ascension of Our Lord into Heaven (ሉቃስ 24:36-53)
- Third Decade: The Descent of the Holy Spirit at Pentecost (የሐዋርያት ሥራ 2:1-41)
- Fourth Decade: The Assumption of Mary into Heaven (ሉቃስ 1:48-49)
- Fifth Decade: The Coronation of Mary as Queen of Heaven and Earth (ራእይ 12:1)